ማሕልየ መሓልይ 8:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የውሃ ብዛት ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም፣ፈሳሾችም አያሰጥሟትም፤ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉስለ ፍቅር ቢሰጥፈጽሞ ይናቃል።

8. ትንሽ እኅት አለችን፤ጡትም ገና አላወጣችም፤ስለ እርሷ በምንጠየቅበት ቀንምን ማድረግ እንችል ይሆን?

9. እርሷ ቅጥር ብትሆን፣በላይዋ የብር መጠበቂያ ማማ እንሠራባታለን፤በር ብትሆን፣በዝግባ ዕንጨት እንከልላታለን።

10. እነሆ እኔ ቅጥር ነኝ፤ጡቶቼም እንደ ማማ ግንቦች ናቸው፤እኔም በዐይኖቹ ፊት፣ሰላምን እንደሚያመጣ ሰው ሆንሁ።

11. ሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤የወይኑን ተክል ቦታም ለአትክልተኞች አከራየው፤እያንዳንዳቸውም የፍሬውን ዋጋ፣አንድ አንድ ሺህ ሰቅል ብር ያመጡለት ነበር።

ማሕልየ መሓልይ 8