ሚክያስ 4:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በመጨረሻው ዘመን፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ፣ከተራሮች ልቆ ይታያል፤ከኰረብቶች በላይ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።

2. ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ፤በመንገዱ እንድንሄድ፣መንገዱን ያስተምረናል።”ሕግ ከጽዮን ይመጣል፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም።

ሚክያስ 4