መዝሙር 86:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና።

4. የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።

5. ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።

መዝሙር 86