መዝሙር 83:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ

9. በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።

10. እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤እንደ ምድርም ጒድፍ ሆኑ።

11. መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤

12. እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።

መዝሙር 83