መዝሙር 81:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤ለሌላም አምላክ አትስገድ።

10. ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ።

11. “ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ።

12. ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።

13. “ምነው ሕዝቤ ቢያደምጠኝ ኖሮ፣እስራኤል በመንገዴ በሄደ ኖሮ፣

መዝሙር 81