መዝሙር 79:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው?የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን?ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?

6. በማያውቁህ ሕዝቦች ላይ፣ስምህን በማይጠሩ፣መንግሥታት ላይ፣መዓትህን አፍስስ፤

7. ያዕቆብን በልተውታልና፤መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል።

8. የአባቶቻችንን ኀጢአት በእኛ ላይ አትቍጠርብን፤ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፤በጭንቅ ላይ እንገኛለንና።

መዝሙር 79