መዝሙር 78:61-64 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

61. የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።

62. ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።

63. ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።

64. ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።

መዝሙር 78