መዝሙር 74:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ጠላቶችህ በመገናኛ ስፍራህ መካከል ደነፉ፤አርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ።

5. በጫካ መካከል ዛፎችን ለመቍረጥ፣መጥረቢያ የሚያነሣ ሰው መሰሉ።

6. በእደ ጥበብ ያጌጠውን ሥራ ሁሉ፣በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባበሩት።

7. መቅደስህን አቃጥለው አወደሙት፤የስምህንም ማደሪያ አረከሱ።

መዝሙር 74