መዝሙር 72:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።

3. ተራሮች ብልጽግናን፣ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።

4. ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤የድኾችን ልጆች ያድናል፤ጨቋኙንም ያደቀዋል።

5. ፀሓይ እስካለች ድረስ፣ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

6. እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል።

መዝሙር 72