መዝሙር 71:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።

5. ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።

6. ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።

7. ብዙዎች እንደ ጒድ አዩኝ፤አንተ ግን ጽኑ አምባዬ ነህ።

8. ቀኑን ሙሉ ክብርህን ያወራ ዘንድ፣አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል።

መዝሙር 71