መዝሙር 7:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ጋሻዬ ልዑል አምላክ ነው፤እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል።

11. እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው።

12. ሰው በንስሓ የማይመለስ ከሆነ ግን፣ሰይፉን ይስላል፤ቀስቱን ይገትራል።

13. የሚገድሉ ጦር ዕቃዎቹን አሰናድቶአል፤የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አዘጋጅቶአል።

መዝሙር 7