መዝሙር 69:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና።

2. የእግር መቆሚያ በሌለው፣በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ሞገዱም አሰጠመኝ።

3. በጩኸት ደከምሁ፤ጉሮሮዬም ደረቀ፤አምላኬን በመጠባበቅ፣ዐይኖቼ ፈዘዙ።

መዝሙር 69