መዝሙር 66:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ

8. ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።

9. እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።

10. አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤እንደ ብርም አነጠርኸን።

መዝሙር 66