መዝሙር 51:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እኔም ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፤ኀጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።

14. የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።

15. ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት፤አፌም ምስጋናህን ያውጃል።

16. መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ ባቀረብሁልህ ነበር፤የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም።

መዝሙር 51