መዝሙር 51:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ መጠን፣ምሕረት አድርግልኝ፤እንደ ርኅራኄህም ብዛት፣መተላለፌን ደምስስ።

2. በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ፤ከኀጢአቴም አንጻኝ።

3. እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፤ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው።

መዝሙር 51