መዝሙር 40:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።”

9. በታላቅ ጉባኤ ውስጥ ጽድቅን አበሠርሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እንደምታውቀው፣ከንፈሮቼን አልገጠምሁም።

10. ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ምሕረትህንና እውነትህን፣ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።

መዝሙር 40