መዝሙር 27:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ልቤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።

9. ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤መቼም ረዳቴ ነህና።አዳኝ አምላኬ ሆይ፤አትጣለኝ፤ አትተወኝም።

10. አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር ይቀበለኛል።

መዝሙር 27