መዝሙር 26:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤

7. የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።

9. ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋር፣ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋር አታስወግዳት።

10. በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ፤ቀኝ እጃቸውም ጒቦን ያጋብሳል።

መዝሙር 26