መዝሙር 23:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤አንዳች አይጐድልብኝም።

2. በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤

3. ነፍሴንም ይመልሳታል።ስለ ስሙም፣በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።

መዝሙር 23