መዝሙር 21:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ዘራቸውን ከምድር፣ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።

11. ክፋት ቢያስቡብህ፣ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤

12. በመጡበት ትመልሳቸዋለህና፤ቀስትህንም በፊታቸው ላይ ታነጣጥራለህ።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል፤ኀይልህን እናወድሳለን፤ እንዘምራለንም።

መዝሙር 21