መዝሙር 20:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድንአሁን ዐወቅሁ፤የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።

7. እነዚህ በሰረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤እኛ ግን ትምክህታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።

8. እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤እኛ ግን ተነሣን፤ ጸንተንም ቆምን።

9. እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤እኛም በጠራንህ ቀን ስማን።

መዝሙር 20