መዝሙር 18:39-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

39. አንተ ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፤ባላንጦቼ እግሬ ላይ እንዲደፉ አደረግህ።

40. ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው እንዲሸሹ አደረግህ፤እኔም የሚጠሉኝን አጠፋኋቸው።

41. ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አላገኙም፤ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም አልመለሰላቸውም።

42. ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤እንደ መንገድ ላይ ጭቃም አውጥቼ ጣልኋቸው።

መዝሙር 18