መዝሙር 121:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ፣ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።

5. እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።

6. ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አታመጣብህም።

7. እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ነፍስህንም ይንከባከባታል።

8. እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።

መዝሙር 121