መዝሙር 119:157-163 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

157. የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው፤እኔ ግን ከምስክርህ ዘወር አላልሁም።

158. ቃልህን አይጠብቁምና፣ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ።

159. መመሪያህን እንዴት እንደምወድ ተመልከት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።

160. ቃልህ በሙሉ እውነት ነው፤ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው።

161. ገዦች ያለ ምክንያት አሳደዱኝ፤ልቤ ግን ከቃልህ የተነሣ እጅግ ፈራ።

162. ትልቅ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፤በቃልህ ደስ አለኝ።

163. ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ፤ሕግህን ግን ወደድሁ።

መዝሙር 119