መዝሙር 119:154-158 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

154. ተሟገትልኝ፤ አድነኝም፤እንደ ቃልህም ሕያው አድርገኝ።

155. ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።

156. እግዚአብሔር ሆይ፤ ርኅራኄህ ታላቅ ነው፤እንደ ሕግህ ሕያው አድርገኝ።

157. የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው፤እኔ ግን ከምስክርህ ዘወር አላልሁም።

158. ቃልህን አይጠብቁምና፣ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ።

መዝሙር 119