መዝሙር 119:150-156 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

150. ደባ የሚያውጠነጥኑ ወደ እኔ ቀርበዋል፤ከሕግህ ግን የራቁ ናቸው።

151. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ቅርብ ነህ፤ትእዛዛትህም ሁሉ እውነት ናቸው።

152. ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው፣ከጥንት ምስክርነትህ ተረድቻለሁ።

153. ሕግህን አልረሳሁምና፣ ሥቃዬን ተመልከት፤ ታደገኝም።

154. ተሟገትልኝ፤ አድነኝም፤እንደ ቃልህም ሕያው አድርገኝ።

155. ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።

156. እግዚአብሔር ሆይ፤ ርኅራኄህ ታላቅ ነው፤እንደ ሕግህ ሕያው አድርገኝ።

መዝሙር 119