መዝሙር 116:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣እምነቴን ጠብቄአለሁ።

11. ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።

12. ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

13. የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

14. በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።

መዝሙር 116