መዝሙር 107:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ተራቡ፤ ተጠሙ፤ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።

6. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

7. ወደሚኖሩባትም ከተማ፣በቀና መንገድ መራቸው።

8. እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

9. እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቶአልና፤የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቦአል።

መዝሙር 107