መዝሙር 107:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ከጨለማና ከጥልማሞት አወጣቸው፤እስራታቸውንም በጠሰላቸው።

15. እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

16. እርሱ የናሱን በሮች ሰብሮአልና፤የብረቱንም መወርወሪያ ቈርጦአል።

17. አንዳንዶቹ ከዐመፃቸው የተነሣ ቂሎች ሆኑ፤ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ገቡ።

መዝሙር 107