መዝሙር 105:21-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. የቤቱ ጌታ፣የንብረቱም ሁሉ አስተዳዳሪ አደረገው፤

22. ይኸውም ሹማምቱን በራሱ መንገድ ይመራ ዘንድ፣ታላላቆቹንም ጥበብ ያስተምር ዘንድ ነበር።

23. እስራኤል ወደ ግብፅ ገባ፤ያዕቆብ በካም ምድር መጻተኛ ሆነ።

24. እግዚአብሔር ሕዝቡን እጅግ አበዛ፤ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው፤

25. ሕዝቡን እንዲጠሉ፣በባሪያዎቹም ላይ እንዲያሤሩ ልባቸውን ለወጠ።

መዝሙር 105