መክብብ 7:22-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ብዙ ጊዜ አንተ ራስህ፣ሌሎችን እንደረገምህ ልብህ ያውቃልና።

23. እኔም ይህን ሁሉ በጥበብ ፈትኜ፣“ጠቢብ ለመሆን ቈርጫለሁ” አልሁ፤ይህ ግን ከእኔ የራቀ ነበር።

24. ጥበብ ምንም ይሁን ምን፣እጅግ ጥልቅና ሩቅ ነው፤ማንስ ሊደርስበት ይችላል?

25. ስለዚህ ጥበብንና የነገሮችን አሠራር ለመመርመርና ለማጥናት፣የክፋትን መጥፎነት፣የሞኝነትንም እብደት ለማስተዋል፣አእምሮዬን መለስሁ።

መክብብ 7