መክብብ 4:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ደግሞም ሁለቱ አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ነገር ግን አንዱ ብቻውን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?

12. አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።

13. ምክርን መቀበል ከማያውቅ ሞኝና ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ጠቢብ የሆነ ድኻ ወጣት ይሻላል።

14. ወጣቱ ከእስር ቤት ወደ ንጉሥነት የመጣ ወይም በግዛቱ ውስጥ በድኽነት የተወለደ ሊሆን ይችላል።

መክብብ 4