መክብብ 12:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ልጄ ሆይ፤ ከዚህ ሁሉ በላይ በማንኛውም ነገር ተጠንቀቅ፤ አንዳችም አትጨምር።ብዙ መጻሕፍትን መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ ብዙ ማጥናትም ሰውነትን ያደክማል።

13. እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤እግዚአብሔርን ፍራ፤ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።

14. መልካምም ይሁን ክፉ፣ስውር የሆነውን ነገር ሁሉ አንድ ሳይቀር፣ማንኛውንም ሥራ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።

መክብብ 12