ሕዝቅኤል 7:22-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ፊቴን ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ እነርሱም የከበረውን ቦታዬን ያረክሳሉ፤ ወንበዴዎች ይገቡበታል፤ ያረክሱታልም።

23. “ ‘ምድር በደም መፋሰስ፣ ከተማዪቱም በዐመፅ ተሞልታለችና ሰንሰለት አዘጋጅ።

24. እጅግ የከፉትን ከአሕዛብ አምጥቼ ቤቶቻቸውን እንዲነጥቁ አደርጋለሁ፣ የኀያላኑንም ትዕቢት አጠፋለሁ፤ መቅደሳቸውም ይረክሳል።

25. ሽብር በመጣ ጊዜ ሰላምን ይሻሉ፤ ነገር ግን አያገኟትም።

ሕዝቅኤል 7