ሕዝቅኤል 48:32-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. “ ‘በምሥራቅ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የዮሴፍ በር፣ የብንያም በርና የዳን በር ናቸው።

33. “ ‘በደቡብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች አሉ፤ እነዚህም የስምዖን በር፣ የይሳኮር በርና የዛብሎን በር ናቸው።

34. “ ‘በምዕራብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የጋድ በር፣ የአሴር በርና የንፍታሌም በር ናቸው።

ሕዝቅኤል 48