ሕዝቅኤል 28:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ወደ ጒድጓድ ያወርዱሃል፤በጥልቁም ባሕር ውስጥ፣በባሕሮችም ልብ ውስጥ አስከፊ ሞት ትሞታለህ።

9. ታዲያ በገዳዮችህ ፊት፣“አምላክ ነኝ” ትላለህን?በገዳዮችህ እጅ ስትገባ፣አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

10. በባዕዳን እጅ፣ያልተገረዙትን ሰዎች አሟሟት ትሞታለህ፤እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

11. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

12. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ጥበብን የተሞላህ፣ ፍጹም ውበትን የተላበስህ፣የፍጹምነት ምሳሌ ነበርህ።

ሕዝቅኤል 28