7. “ ‘የሰው ደም በመካከሏ አለ፤በገላጣ ዐለት ላይ አደረገችው እንጂ፣ዐፈር ሊሸፍነው በሚችል፣በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
8. ቍጣዬ እንዲነድና ለመበቀል እንዲያመቸኝ፣ይሸፈንም ዘንድ እንዳይችል፣ደሟን በገላጣ ዐለት ላይ አፈሰስሁ።
9. “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!እኔም ደግሞ የምትቃጠልበትን ማገዶ እቈልላለሁ።
10. ማገዶውን ከምርበት፤እሳቱን አንድድ፤ቅመም ጨምረህበት፣ሥጋውን በሚገባ ቀቅል፤ዐጥንቱም ይረር።