21. ሰብስቤአችሁ የቍጣዬን እሳት በእስትንፋሴ አነድባችኋለሁ፤ እናንተም በዚያ ውስጥ ቀልጣችሁ ትቀራላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።
22. ብር በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፣ እናንተም በከተማዋ ውስጥ ትቀልጣላችሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።’ ”
23. የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
24. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ምድሪቱን፣ ‘አንቺ ያልነጻሽ በቍጣም ቀን ዝናብ ያላገኘሽ ምድር ነሽ’ በላት።