ሕዝቅኤል 21:30-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ሰይፉን ወደ ሰገባው መልሰው፤በተፈጠርህበት ምድር፣በተወለድህበትም አገር፣በዚያ እፈርድብሃለሁ።

31. መዓቴን በላይህ አፈሳለሁ፤የቍጣዬንም እሳት አነድብሃለሁ፣በጥፋት ለተካኑ፣ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ።

32. ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ፣ደምህ በምድርህ ይፈሳል፣ከእንግዲህ መታሰቢያ አይኖርህም፤እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና።’ ”

ሕዝቅኤል 21