ሕዝቅኤል 16:54-56 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

54. ይህም የሚሆነው ለእነርሱ መጽናኛ በመሆንሽ እንድ ትዋረጂና ባደረግሽው ሁሉ እንድታፍሪ ነው።

55. እኅቶችሽ ሰዶምና ሴት ልጆቿ እንዲሁም ሰማርያና ሴት ልጆቿ ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ ይመለሳሉ፤ አንቺና ሴት ልጆችሽም ቀድሞ ወደ ነበራችሁበት ሁኔታ ትመለሳላችሁ።

56. በታበይሽበት ወቅት የእኅትሽን የሰዶምን ስም ለመጥራት እንኳ ፈቃደኛ አልነበርሽም፤

ሕዝቅኤል 16