29. ርኵሰትሽንም እስከ ነጋዴዎች ምድር እስከ ባቢሎን ድረስ አበዛሽ፤ ያም ሆኖ አልረካሽም።
30. “ ‘እንደ ዐይን አውጣ አመንዝራ ይህን ሁሉ መፈጸምሽ ምን ዐይነት ደካማ ልብ ቢኖርሽ ነው! ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
31. በየመንገዱ መጠምዘዣ ላይ ጒብታሽን ባበጀሽና በየአደባባዩም መስገጃ ኰረብታ በሠራሽ ጊዜ እንደ ማንኛውም ዝሙት አዳሪ አልነበርሽም፤ ምክንያቱም ዋጋ አላስከፈልሽም።
32. “ ‘አንቺ ከገዛ ባሏ ይልቅ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ነሽ!