ሐዋርያት ሥራ 5:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ጒልማሶችም ተነሥተው አስከሬኑን ገነዙት፤ ወስደውም ቀበሩት።

7. ሦስት ሰዓት ያህልም ካለፈ በኋላ፣ ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ መጥታ ገባች።

8. ጴጥሮስም፣ “እስቲ ንገሪኝ፤ መሬታችሁን የሸጣችሁት በዚህ ዋጋ ነውን?” አላት።እርሷም፣ “አዎን፤ በዚሁ ዋጋ ነው” አለች።

9. ጴጥሮስም፣ “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ እንዴት እንዲህ ተስማማችሁ? እነሆ፤ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች ተመልሰው እግራቸው ደጃፍ ላይ ነው፤ አንቺንም ይዘው ይወጣሉ” አላት።

10. እርሷም ወዲያውኑ እግሩ ሥር ወድቃ ሞተች፤ ጒልማሶቹም ሲገቡ ሞታ አገኟት፤ አውጥተውም በባሏ አጠገብ ቀበሯት።

ሐዋርያት ሥራ 5