ሉቃስ 8:50-53 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

50. ኢየሱስም ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፣ “አይዞህ አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ ልጅህ ትድናለች” አለው።

51. ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሲገባም ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና እናት በቀር ማንም አብሮት እንዲገባ አልፈቀደም።

52. በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።

53. ሰዎቹም መሞቷን ስላወቁ ሣቁበት።

ሉቃስ 8