ሉቃስ 1:62-65 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

62. አባቱንም ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት።

63. እርሱም መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ለምኖ፣ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም በነገሩ ተደነቁ።

64. ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱ ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ መናገር ጀመረ።

65. ጎረቤቶቹም ሁሉ በፍርሀት ተሞሉ፤ ይህም ሁሉ ነገር በደጋማው የይሁዳ ምድር ሁሉ ተወራ።

ሉቃስ 1