2 ተሰሎንቄ 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና።

11. ከእናንተ አንዳንዶች ሥራ ፈቶች እንደሆኑ ሰምተናል፤ እነርሱም ያለ ሥራ እየዞሩ በሰው ጒዳይ ጣልቃ የሚገቡ ናቸው።

12. እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተግተው ሥራቸውን እንዲሠሩና እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።

13. እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፤ መልካም ሥራን ከመሥራት ከቶ አትታክቱ።

14. በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።

2 ተሰሎንቄ 3