2 ሳሙኤል 23:24-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙ ባቸዋል፤የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

25. አሮዳዊው ሣማ፣አሮዳዊው ኤሊቃ፣

26. ፈሊጣዊው ሴሌስ፣የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣

27. ዓናቶታዊው አቢዔዜር፤ኩሳታዊው ምቡናይ፣

28. አሆሃዊው ጸልሞን፣ነጦፋዊው ማህራይ፣

29. የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፣ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣

2 ሳሙኤል 23