1 ዮሐንስ 5:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይጸልይ፤ እግዚአብሔርም ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ላደረጉት ሕይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃም ኀጢአት አለ፤ ስለዚህኛው ግን ይጸልይ አልልም።

17. ዐመፅ ሁሉ ኀጢአት ነው፤ ለሞት የማያበቃም ኀጢአት አለ።

18. ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት እንደማያደርግ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚጠብቀው፣ ክፉውም እንደማይነካው እናውቃለን።

19. እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ መላው ዓለምም በክፉው ሥር እንደሆነ እናውቃለን።

1 ዮሐንስ 5