1 ዜና መዋዕል 2:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።

20. ሆር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።

21. ከዚያም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።

22. ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።

1 ዜና መዋዕል 2