1 ነገሥት 18:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አክዓብም የቤተ መንግሥቱን አዛዥ አብድዩን ጠራው፤ አብድዩም እግዚአብሔርን በጣም የሚፈራ ሰው ነበር።

4. ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያስገደለች በነበረበት ጊዜ፣ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በሁለት ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይሰጣቸው ነበር።

5. አክዓብም አብድዩን፣ “ተነሣና በአገሪቱ ውስጥ ወዳሉት ምንጮችና ሸለቆዎች ሂድ፤ ፈረሶቻችንና በቅሎዎቻችን እንዳይሞቱ በሕይወት እንዲቈዩ ምናልባት ሣር እናገኝ ይሆናል።” አለው።

6. ስለዚህ የሚሄዱበትን ምድር ተከፋፈሉ፤ አክዓብ በአንድ በኩል፣ አብድዩም በሌላ በኩል ሄደ።

1 ነገሥት 18