1 ነገሥት 12:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ንጉሡም በሽማግሌዎቹ የተሰጠውን ምክር ትቶ፣ ሕዝቡን የሚያስከፋ መልስ ሰጣቸው፤

14. ወጣቶቹ የሰጡትን ምክርም ተቀብሎ፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ ከዚያ ይብስ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።

15. እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም የተናገረው ቀድሞውኑ እግዚአብሔር የወሰነው ስለ ሆነ፣ መፈጸም ነበረበትና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።

1 ነገሥት 12